በአማራ ክልል ከ90 በመቶ በላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ መሰራቱ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ከ90 በመቶ በላይ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ መሰራቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡
በክልሉ ጥር 6 ቀን 2014 ዓ.ም የተጀመረው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ የንቅናቄ ስራ ርክክብ ተደርጓል።
ርክክቡ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ወረዳ የተደረገ ሲሆን ፥ በወረዳው ያለው ህብረተሰብ ከህልውና ዘመቻው ጋር እየታገለ የተሻለ ተሞክሮ መገኘቱ አስደናቂ መሆኑ ተገልጿል።
የክልሉ ግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሀይለማርያም ከፋያለው ፥ በክልሉ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራ ከ250 ሺህ በላይ በሆነ ሄክታር መሬት አርሶ አደሩ ተሣትፎ ያደረገበት የተፈጥሮ ሀብት ስራ ለመስራት ከታቀደው ከ90 ከመቶ በላይ መሳካቱን ተናግረዋል፡፡
የተፈጥሮ ሀብት ስራውም የስነ ህይወት ብዝሃ ሕይወት ላይ የሚኖረው ሚና ከፍ ያለ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊሠራ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
በኤልያስ አንሙት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!