ዓለምአቀፋዊ ዜና

የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ሚኒስትር ስልክ ተጠለፈ

By Tibebu Kebede

February 27, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ሚኒስትር አያንዳ ድሎድሎ እና የምክትላቸው ስልክ መጠለፉ ተሰምቷል፡፡

የሃገሪቱ መርማሪዎች የደህንነት ሚኒስትሯ ስልክ እና የሌሎች ባርደረቦቻቸው ስልክ እንዴት እንደተጠለፈ በማጣራት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

መረጃ መዝባሪዎቹ  የድርጅቱን ልዩ ልዩ ሰነዶች እና የተለያዩ የሃገር ውስጥ እና የሌላ ሃገራት ገንዘቦችን መመዝበራቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ ከሳምንታት በፊት በዋና ከተማዋ ፕሪቶሪያ የደቡብ አፍሪካ የደህንነት ኤጀንሲ ላይ ዝርፊያ ተፈጽሞ እንደነበር በዘገባው ተመላክቷል።

ባለፈው ዓመት መረጃ መዝባሪዎች የፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳን ከምርጫ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ኢሜሎች በመጥለፍ ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ