የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

By Tibebu Kebede

February 27, 2020

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን ለግብጹ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ ኤል ሲሲ ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት ገልጸዋል።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በራሳቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግስት ስም ባስተላለፉት የሀዘን መግለጫ መልዕክት፥ የቀድሞው የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረከ ለሀገራቸው እድገት ብዙ የሰሩ መሆናቸውን አውስተዋል።