በመስጠትና ማካፈል ትውልድን መገንባት ይቻላል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመስጠትና ማካፈል ትውልድን መገንባት የሚቻል መሆኑን ዛሬ በአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በተካሄደ የመጻሕፍት ርክክብ መርሐ ግብር ላይ ተናገሩ፡፡
በመጻሕፍት ርክክቡ ሥነ ስርዓት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር÷ ከቀናት በኋላ ለአንድ ወር የሚቆይ በርከት ያሉ መጻሕፍትን ለማሰባሰብ መታቀዱን ገልጸው ኢትዮጵያውያን አሁንም የመጻሕፍት አበርክቷቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
መጻሕፍትን ላበረከቱ ግለሰቦችም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ባለፉት 3 ወራት 12 ሺህ መጻሕፍት ለአብርሆት ቤተ መጻሕፍት በበጎ ፈቃደኞች ተበርክቷል፡፡
በዛሬው እለትም ከሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ያበረከቷቸው 7 ሺህ 388 መጻሕፍት ርክክብ በአብርሆት ቤተ መጸሃፍት ተካሂዷል።
መጻሕፍቱ በተለያዩ ዘርፎች በርካታ አገልግሎት የሚሰጡ መሆናቸው ተመላክቷል።
ቤተልሔም ሰለሞን የተባሉ በእንግሊዝ ሀገር የፒ ኤች ዲ ተማሪ በራሳቸው ተነሳሽነት 5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ግምትያላቸው 5 ሺህ 200 መጻሕፍት እንዲሁም አምባሳደር ማርቆስ የተባሉ በጡረታ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ 904 መጻሕፍት አበርክተዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበሩ እና አሁን በህይወት የሌሉ ግለሰብ ቤተሰቦች 997 እንዲሁም ማይክሮሊንክ ኮሌጅ ደግሞ 287 መጻሕፍት አበርክተዋል።
መጻሕፍቱን ማሰባሰብ የተቻለው በጠቅላይ ሚኒስትሩ በተቋቋመ ኮሚቴ አማካኝነት መሆኑ ታውቋል፡፡
አብርሆት ቤተ መጻሕፍት 4 ሚሊየን መጻሕፍት እንደሚያስፈልጉት ተመላክቷል፡፡
በፍሬህይወት ሰፊው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!