Fana: At a Speed of Life!

በጅማ ከተማ አዲስ ደረቅ ወደብና ተርሚናል ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዘጠነኛ የደረቅ ወደብና ተርሚናል መዳረሻውን በጅማ ከተማ እንደሚገነባ አስታወቀ፡፡
በጅማ ከተማ የሚገነባው ደረቅ ወደብና ተርሚናል በምዕራቡ የኢትዮጵያ ክፍል ለሚገኙ ተገልጋዮች በቅርበት አገልግሎት በመስጠት የወጪና ገቢ ንግዱን ለማሳለጥ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
በተለይ አካባቢው በቡናና በሌሎችም የግብርና ምርቶች በእጅጉ የሚታወቅ በመሆኑ እነዚህ የግብርና ምርቶች ቀልጣፋ የሎጂስቲክስ አገልግሎት አግኝተው ለውጭ ገበያ እንዲደርሱ በማስቻል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡
የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክና አየር መንገድን ማዕከል አድርጎ ከጅማ ወደ ቦንጋ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ ለደረቅ ወደቡ ግንባታ የሚሆን 20 ሄክታር መሬት መመረጡን ከባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ድርጅቱ ለመሬቱ የካሳ ክፍያና መሰል ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ሂደት ላይ እንደሆነና የመሬት ርክክቡ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚከናወን መሆኑን በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የወደብና ፋሲሊቲ ልማት መምሪያ ኢንጂነር አሰፋ ወርቅነህ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ስምንት ወደብና ተርሚናሎች ያሉት ሲሆን በጅማ ከተማ የሚገነባው ዘጠነኛው መሆኑ ታውቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.