“የፈተናዎች መብዛት ከብልጽግና ጉዟችን አያግደንም” በሚል መሪ ሃሳብ የወጣቶች የውይይት መድረክ በባሕርዳር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፈተናዎች መብዛት ከብልጽግና ጉዟችን አያግደንም በሚል መሪ ሃሳብ የወጣቶች የውይይት መድረክ በባሕርዳር ተካሂዷል፡፡
በምክክር መድረኩ የባሕርዳር ከተማ ወጣቶች እና የከተማዋ የሥራ ኃላፊዎች ከከተማዋ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
የባሕርዳር ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ በሪሁን መንግስቱ በመክፈቻ ንግግራቸው ÷ የብልጽግና ፓርቲ ፈተናዎችን እየተሻገረ እዚህ መድረሱን አንስተው በቀጣይም መልካም ጎኖችን እያጠናከሩ ድክመቶችን እያረሙ የሚደረገው ጉዞ ይቀጥላል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የብልጽግና ፓርቲ መልካም ጅምሮች እና ፈተናዎች ላይ የመነሻ ጽሁፍ ቀርቧል፡፡
ለመወያያነት በቀረበው ጽሁፍ ÷ያለፉት ዘመናት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፈተናዎች፣ ብልጽግና ፈተናዎችን ለመፍታት ያደረጋቸው ጥረቶች እንዲሁም ሀገር በቀጣይ ወደ ተሻለ ዲሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት መግባት በምትችልባቸው አቅጣጫዎች ላይ ሃሳብ ቀርቧል።
በባሕርዳር እየተካሄደ ያለው ጉባኤ የብልጽግና ፓርቲ ካካሄደው 1ኛ ጉባኤ በኋላ ሲካሄድ የቆየው ሕዝባዊ ውይይት አካል መሆኑ ተነግሯል።
በለይኩን ዓለም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!