ስፓርት

ፋሲል ከነማ ከአሠልጣኙ ስዩም ከበደ ጋር በሥምምነት ተለያየ

By Alemayehu Geremew

April 09, 2022

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 1፣2014(ኤፍ ቢ ሲ) የአምናው ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ ከአሠልጣኙ ስዩም ከበደ ጋር በሥምምነት ተለያይቷል።

ያለፉትን ሁለት ዓመታት ከመንፈቅ አፄዎቹን በዋና አሠልጣኝነት የመሩት ስዩም ከበደ ክለቡ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫ እንዲያነሳ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጅ ቡድኑ በዘንድሮው የውድድር ዓመት የውጤት ቀውስ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ የክለቡ ቦርድ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ክለቡ ከአሠልጣኝ ስዩም ከበደ ጋር እንዲለያዩ ወስኗል፡፡

በትናንትናው ዕለትም ክለቡ በአዳማ ከተማ ባረፈበት ሆቴል ለአሰልጣኝ ስዩም ከበድ ሽኝኝት እንደረገለት ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።

የዋና አሠልጣኙን ስንበት ተከትሎ ክለቡ በቀጣይ የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች በምክትል አሠልጣኝ የሚመራ ይሆናል፡፡