Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አቶ አህመድ ሺዴ አስታወቁ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ አስታወቁ፡፡

ሚኒስትሩ በደቡብ ሱዳን የገንዘብና ፕላን ሚኒስትር አጋክ አቹል ከተመራ ልዑካን ጋር የተወያዩ ሲሆን÷ በሁለቱ አገራት መካከል የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ እንደሚዋቀር ተገልጿል፡፡

አገራቱ በኮሚሳ እና በኢጋድ እንዲሁም በአለም አቀፍ ተቋማት መካከል በሚደረጉ ግንኙነቶች በፋይናንስ እና በቴክኒክ በጋራ ለመሰራት ተሰማምተዋል፡፡

ሁለቱ እህትማማች አገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታቸው በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ መሆኑን የገለጹት አቶ አህመድ ሺዴ÷ በተለይም በኢኮኖሚ፣ በንግድ እና በጉምሩክ፣ በመሰረተ ልማት እና በሃይል አቅርቦት በትብብር እየሰሩ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን አንድነትና ዘላቂ ሠላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የበኩሏን አሰተዋጽኦ  እንደምታበረክት ጠቅሰው÷ በሀገራቱ መካከል በመሰረተ ልማት ዘርፍ እየተደረጉ ያሉ ግንኙነቶች፣ የነዳጅ ግዢና ሽያጭ እንዲቀላጠፍ  እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚ እና በፓለቲካዊ መስኮች ማሻሻያዎች እያደረገች መሆኑን ለከፍተኛ ልዑካን ቡድኑ ያስረዱት አቶ አሕመድ÷ በባንኩ ዘርፍ የውጭ አገራት ኩባንያዎች እንዲሳተፉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወነ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

የደቡብ ሱዳን ገንዘብና ፕላን ሚኒስትር አጋክ አቹል ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን በኢኮኖሚ፣ በሰላምና ደህንነት እያደረገች ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል፡፡ በቀጣይም ሁለቱ አገራት ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ የሚንስትሮች የጋራ ኮሚቴ መዋቀሩን ማወደሳቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.