Fana: At a Speed of Life!

በነገው ዕለት “ለመስቀሉ እሮጣለሁ” በሚል መሪቃል ይካሄዳል የተባለው ሩጫ ከሚመለከተው አካል ሕጋዊ እውቅና ያላገኘ ነው – የአዲስ አበባ ፖሊስ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ነገ “ለመስቀሉ እሮጣለሁ” በሚል መሪቃል ይካሄዳል የተባለው ሩጫ ከሚመለከተው አካል ሕጋዊ እውቅና ያላገኘ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ነገ ሚያዚያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም “ለመስቀሉ እሮጣለሁ” በሚል ምክንያት በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚካሄድ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል ብሏል።
የሩጫ ውድድሩ ማሟላት የሚገባውን ሕጋዊ እውቅና ከሚመለከተው አካል ያላገኘ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ፖሊስ ባወጣው መግለጫ ነገ ሚያዚያ 2 ቀን 2014 ዓ.ም “ለመስቀሉ እሮጣለሁ” በሚል ምክንያት በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚካሄድ ሀሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ ይገኛል ብሏል።

የሩጫ ውድድሩ ማሟላት የሚገባውን ሕጋዊ እውቅና ከሚመለከተው አካል ያላገኘ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም በመዲናዋ የተካሄዱ የጎዳና ላይ ሩጫዎች በተቀናጀ ሁኔታ በመመራታቸው ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቃቸውን ያስታወሰው ፖሊስ÷ የጎዳና ላይ ሩጫን ለማካሄድ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፎ እና ዝግጅት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ከሚመለከተው አካል ህጋዊ የእውቅና ፈቃድ ማግኘት ግዴታ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ይሁን እንጅ በድንገት የጎዳና ላይ ሩጫ ለማካሄድ የሚደረግ እንቅስቃሴ በከተማው የፀጥታ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ የሚፈጥር መሆኑን ህብረተሰቡም ሆነ ሩጫውን ያዘጋጁ አካላት ሊገነዘቡ ይገባልም ነው ያለው።

ሩጫው ይደረግበታል በተባለበት ቀን ቀድሞ የታቀዱ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን ፕሮግራም የተያዘ መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ÷ የፀጥታ ኃይሉ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ሳያደርጉ በድንገት ሩጫ እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲታቀቡም አሳስቧል፡፡

የተዛባ መረጃ የሚያስተላልፉ አካላት ከህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲታቀቡ እና ይህንን መልዕክት በመተላለፍ ለሚፈጠር ማንኛውም ችግር ሩጫውን እናስተባብራለን የሚሉ አካለት በህግ እንደሚጠየቁም ነው ያስታወቀው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.