Fana: At a Speed of Life!

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤትን ጎበኙ፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘው ተሻገርና እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ አፈ ጉባኤዎች፣ ሚኒስትሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ፌዴራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤትን ጎብኝተዋል።
ሃላፊዎቹ የተቋሙን የህንፃ ዕድሳትን፣ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎች፣ ዳጂታል የሬዲዮ መገናኛዎች፣ የደህንነት ካሜራዎችና ሌሎች የፖሊስ አገልግሎት ቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ጎብኝተዋል።
መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተቋሙን መጎብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን፤ በወቅቱ ፖሊስ ዘመናዊ ሰራዊት እንዲሆን የጀመርነውን ሪፎርም አጠናክረን የምንቀጥልና የፌደራል መንግሥት ሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አረጋግጣለሁ ማለታቸው ይታወሳል።
ፖሊስ እንደ ህግ አስከባሪ ህግ ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንደ ወንጀል መርማሪ የወንጀል ምርመራ ክህሎት ያለው፣ የስነ-ባህሪ ጥናት ያጠና እንዲሁም ‘ቢሄቪየራል ሳይኮሎጂን ጠንቅቆ የሚያውቅ እንዲሆን የተጀመረው ሪፎርም እንደሚቀጥልም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.