Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ 2 – አሰላ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ ጥገና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በዘራፊዎች ተቆርጦ የወደቀው ከአዋሽ 2 ወደ አሰላ የተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን በእንጨት ምሰሶ የመተካት ሥራ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።
መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በዶዶታ ወረዳ እና ጌራ ከተማ አቅራቢያ በተፈፀመው የምሰሶ አካላት ዝርፊያ ሁለት ምሰሶዎች የወደቁ ሲሆን ÷በአካባቢው በከፊል ኤሌክትሪክ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል።
ለቀናት ሲከናወን የቆየው ጥገና ዛሬ በመጠናቀቁም ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ኤሌክትሪክ መልሶ የማገናኘት ሥራ እንደሚከናወን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.