Fana: At a Speed of Life!

ጉዳት የደረሰባቸውን ከተሞች መልሶ ለማቋቋም ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባ ቢሮው አሳሰበ

አዲስ  አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወራሪው የህወሀት ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ከተሞች መልሶ ለማቋቋም ሁሉም አካላት ርብርብ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአማራ ክልል ከተሞችና መሰረተ ልማት ቢሮ አሳሰበ፡፡
ቢሮው ˝ከተሞችን የብልጽግና ማዕከል እናደርጋለን “ በሚል መሪ ሀሳብ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በክልሉ የከተሞች መስፋፋት በስፋት እየታየ መሆኑን የገለጹት የቢሮው ሀላፊው አቶ ቢያዝን እንኳሆነ÷በ2001ዓ.ም በክልሉ 231 ከተሞች እንደነበሩ ጠቅሰው÷ አሁን ላይ ከ660 በላይ ደርሰዋል ብለዋል።
ይህም በክልሉ የከተሞች እድገት በየዓመቱ 33% ከመቶ እድገት እያሳየ መሆኑን ያመላክታል ነው ያሉት፡፡
በየዓመቱ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ሰዎች ወደ ከተሞች ይሰፍራሉ ያሉት የቢሮ ሀላፊው÷ ማህበረሰቡን የሚመጥን መሰረተ ልማት እውን ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።
በተለይም ጉዳት የደረሰባቸውን ከተሞች መልሶ በመገንባት የከተሞችን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አመላክተዋል።
በከተሞች የሚታየውን ህገ ወጥ ድርጊት በማስተካከልና የቤቶች ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ያሉት ደግሞ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ አማረ ሰጤ ናቸው፡፡
የዓለም ባንክ በጀትን የሚጠቀሙ ተቋማት ውጤታማ የመሠረተ ልማት ተግባሮችን ሊያከናውኑ ይገባል ብለዋል።
በዘርፉ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ማስተካከል እንደሚገባም አሳስበዋል።
በከድር መሀመድ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.