Fana: At a Speed of Life!

በፍትህ ዘርፉ የሚስተዋሉችግሮችን መፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፍትህ ዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ከፌዴራልና ከክልል የፍትህ አካላት ጋር አገራዊ የጋራ የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡
 
በመድረኩ የፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ደግፌ ቡላን ጨምሮ የሲዳማ ክልል የፍትህ ቢሮ ሀላፊ አቶ ማቶ ማሩ እና የፍትህ አካላት ተገኝተዋል፡፡
 
ችግር ፈቺ የሆኑ ጥናትና ምርምሮችን በመስራት ቅንጅታዊ አሰራር እንዲኖር ማድረግ እና መደገፍ የኢንስቲትዩቱ ትኩረት መሆኑን ዳይሬክተሩ አምባሳደር ደግፌ ቡላ ተናግረዋል፡፡
 
የህብረተሰቡን የፍትህ ችግር ሊፈቱ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው÷ ክልሎችም በዚህ የምክክር መድረክ የጋራ አስተሳሰብ በመፍጠር የህብረተሰቡ የፍትህ ችግር እንዲፈታ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡
 
በደቡብ፣ በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች በፍትህና በህግ ምርምር ማሰልጠኛ ተቋማት የተከናወኑ ተግባራት ላይም ውይይት ተካሂዷል፡
 
መድረኩ በፌዴራልና በክልል የፍትሕ አካላት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን በመዘርጋት በፍትህ ዘርፉ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያስችል መገለፁት ከፌዴራል የፍትሕና የሕግ ኢንስቲትዩት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.