Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም ከአምሥት ድርጅቶች ጋር የአጋርነት ውል ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም የመደበኛ ባለገመድ ኢንተርኔት አገልግሎት በአጋርነት ለማቅረብ ከአምሥት ድርጅቶች ጋር የአጋርነት ውል ተፈራርሟል፡፡

ውል የወሰዱት ድርጅቶችም ”ዌብ ስፕሪክስ አይቲ ሶሉሽን” ፣ ”ቪቫ ቴክ ትሬዲንግ”፣ ”ዘርጋው አይ ኤስ ፒ” ፣ “ስካይ ኔት አይቲ ሶሉሽን” እና ”ዱሌ ቢዝነስ ግሩፕ እንደሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም እና አምሥቱ አጋር ድርጅቶች የተፈራረሙት ሥምምነት ለሦስት ዓመታት የሚጸና ይሆናልም ተብሏል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ድርጅቶቹ የመደበኛ ኢንተርኔት ከፍተኛ “ባንድ ዊድዝ”ን ከኢትዮ ቴሌኮም በመውሰድ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሚገኙ ደንበኞች ለሦስት ዓመታት አገልግሎት ይሰጣሉ ተብሏል።

የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ከሽያጭ ማዕከላቱ በተጨማሪ ከተጠቀሱት አምሥት ድርጅቶች የመደበኛ ኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉም ተገልጿል።

ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ፥ የብሮድ ባንድ አገልግሎት መስፋፋት ሀገራችን ለምትገነባው የዲጂታል ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን ጠቅሰው ፥ ይህንንም ይበልጥ ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ከአጋሮቻችን ጋር በጥምረት እንሰራለን ብለዋል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.