Fana: At a Speed of Life!

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር ክልል መብረር ይችላሉ – የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 3 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እገዳ ተጥሎባቸው የቆዩትን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዛሬ ጀምሮ በኢትዮጵያ አየር ክልል መብረር እንደሚችሉ አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ከዚህ ቀደም መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በረራ ቁጥር ኢ ቲ-302 ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ላይ የደረሰውን አደጋ መሠረት በማድረግ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ሥሪት ተለዋጭ መመሪያ እስካልወጣ ድረስ በኢትዮጵያ አየር ክልል እንዳይበር እገዳ መጣሉ ይታወሳል።
ይሁንና አውሮፕላኑ የተፈበረከበት አገር የአሜሪካ ፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር አውሮፕላኑ ለአደጋው መንስኤ የሆኑ ችግሮችን በመለየት አደጋውን ሊቀርፍ የሚያስችል አስገዳጅ መመሪያ በማውጣት መመሪያዎቹ ተግባራዊ እንደሆኑ አውሮፕላኖቹ ወደ በረራ መመለስ አንደሚችሉ ገልጿል።
በመሆኑም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በአውሮፕላኖቹ ላይ የተደረገውን የዲዛይን ማሻሻያ እና የአየር መንገዱን የበረራ መመሪያዎች እና ሥልጠናዎች በተገቢው ሁኔታ በመፈተሽ አየር መንገዱ መመሪያዋቹን ተግባራዊ ማድረጉን በማረጋገጥ ከዛሬ ጀምሮ ጥሎት የነበረውን የበረራ እገዳ ማንሣቱን አስታውቋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.