Fana: At a Speed of Life!

በ18ኛ ሳምንት ፕሪሚየር ሊግ ሀዲያ ሆሳና ከአርባምንጭ ከተማ ጋር አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 3፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አስገራሚ ትዕይንት ያስተናገደው የሃዲያ ሆሳዕና እና አርባምንጭ ከተማ ጨዋታ 4 አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

8 ጎሎች በተቆጠሩበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ አርባ ምንጭ ከተማ እስከ 80 ደቂቃ ሃዲያ ሆሳናን 4 ለ 1 ሲመራ ቢቆይም ነብሮቹ በ10 ደቂቃዎች ውስጥ በተከታታይ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል፡፡

ለአርባ ምንጭ ከተማ አህመድ ሁሴን 3 ጎሎችን በማስቆጠር ሃት – ትሪክ ሲሰራ ፀጋዬ አበራ ቀሪዋን አንድ ጎል ማስቆጠር ችሏል፡፡

ለሀዲያ ሆሳና ደግሞ ፍኖተየሱስ ተክለብርሃን፣ ሀብታሙ ታደሰ፣ ሄኖክ አፈወርቅ እና ብርሃኑ በቀለ ማስቆጠር ችለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.