Fana: At a Speed of Life!

የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ህብረቱ የፍቺ ቀነ ገደቡን እንዲያራዝም ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሀገሪቱ ከአውሮፓ ህብረት ጋር በይፋ የምትለያይበትን ቀነ ገደብ ህብረቱ እንዲያራዝም ጠየቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሀገራቸው ፓርላማ በፍችው ዙሪያ ያቀረቡት ሃሳብ ውድቅ መድረጉን ተከትሎ ነው ለህብረቱ በፃፉት ድበዳቤ ቀነ ገደቡ እንዲራዘም የጠየቁት።

ቀነ ገደቡ መራዘሙን እረሳቸውም እንደማያምኑበት ለህብረቱ በፃፉት ሌላ ደብዳቤ አሳውቀዋል።

የአውሮፓ ህብረት ድብዳቤው እንደደረሰው ገልፆ ምላሽ ለመስጠት ከህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር እንደሚመክር ነው ያመለከተው።

በእርግጥ ህብረቱ በቀነ ገደቡ መራዘም ላይ ከተስማማ ቀደም ሲል ከተቀመጠው የፈረንጆቹ ጥቅምት 31 ሳናልፍ ከህብረቱ መውጣቷ እርግጥ ነው ሲሉ በነበሩት ጠቅላይ ሚኒስር ቦሪስ ጆንሰን ላይ የሚኖርን እምነት እንደሚሸረሽር ተገምቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.