Fana: At a Speed of Life!

በሐረር ከኢድ እስከ ኢድ እና የሸዋል ኢድ በዓላትን ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኢድ እስከ ኢድ እና የሸዋል ኢድ በዓላትን በተሳካ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የሀረሪ ክልል አስታውቋል፡፡
በሐረሪ ክልል ከኢድ እስከ ኢድ እና የሸዋል ኢድ በዓላት አከባበርና ለበዓሉ የሚመጡ እንግዶች አስፈላጊውን መስተንግዶ እንዲያገኙ ለማስቻል የተቋቋመው አብይ ኮሜቴ በክልሉ ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትን ገምግሟል።
በተለይ ከከተማው ፅዳትና ውበት ጋር ተያይዞ፣ የፕሮጀክት አፈፃፀምን ከማጎልበት አንፃር፣ ሰላምና ፀጥታን ከማጠናከር በዋናነትም ሀይማኖታዊና ባህላዊ ይዘት ያላቸው ኩነቶችን ከማዘጋጀት አንፃር እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች ላይ በሰፊው መክሯል።
ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ ለሚያለሙ ዲያስፖራዎች ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ረገድ እንዲሁም በሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራትንም ኮሚቴው ተመልክቷል፡፡
ከኢድ እስከ ኢድ አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢና የክልሉ ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ እንደተናገሩት በክልሉ አጠቃላይ ከኢድ እስከ ኢድ እና ከሸዋል ኢድ በዓላት ጋር ተያይዞ አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በመሆኑም እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ተግባራት ማጠናከርና ውስንነቶችን በመቅረፍ በተለይም በክልሉ በልዩ ሁኔታ የሚከበረውን የሸዋል ኢድ በዓል አከባበርን የተሳካ እንዲሆን በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከሐረሪ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.