Fana: At a Speed of Life!

መንግሥት የክልሉን ህዝብ ከቀረጥ ነፃ በሆኑ ምግቦች ተጠቃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው – አቶ ሙበሽር ድባድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት የክልሉን ህዝብ ከቀረጥ ነፃ በሆኑ ምግቦች ተጠቃሚ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይና የክልሉ ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙበሽር ድባድ ተናገሩ።
አቶ ሙበሽር ድባድ ምግብን ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት እየተደረገ ባለው ሂደት እና አተገባበር ላይ ከክልሉ ፀጥታ ተቋማት አመራሮች እና ከንግዱ ዘርፍ አጋር አካላት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ህብረተሰቡ በድርቅና በዋጋ ንረት እየተቸገረ ባለበት በዚህ ወቅት፥ መንግሥት የክልሉን ህዝብ ከቀረጥ ነፃ በሆኑ ምግቦች ተጠቃሚ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ይህን ተግባር በማጠናከርና ህብረተሰቡን ከዋጋ ንረት ጋር በተያያዘ ህዝብን በሚያማርሩ ህገወጦች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.