Fana: At a Speed of Life!

አድዋ የሰውነት ማህተም፣ የአንድነታችን ድር እና ማግ በሚል መሪ ቃል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) “አድዋ የሰውነት ማህተም፣ የአንድነታችን ድር እና ማግ” በሚል መሪ ቃል የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።

የምክክር መድረኩን የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጽሃፍት ኤጄንሲ ከሰውኛ ፕሮዳክሽን እና ከአርባ ኤጀንሲ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው።

መሪ ቃሉን መነሻ በማድረግም እስከ የካቲት 23 ቀን ድረስ የሚቆይ የፊልም ፌስቲቫል፣ የመዛግብት ዐውደ ርዕይ እና የሊቃውንት ጉባኤ መርሃ ግብር የተዘጋጀ ሲሆን፥ የዛሬው የምክክር መድረክም የዚሁ አካል ነው ተብሏል።

አድዋ ለምንና እንዴት ተከሰተ፣ ያለው ፋይዳ እና አድዋ የኢትዮጵያውያን ታላቅ የትብብርና የአንድነት ከፍታ ማሳያ በሚሉ ርዕሶች ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

ጥናታዊ ጽሁፎቹ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ነው የቀረቡት።

በፍሬህይወት ሰፊው

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.