በኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ እድገት የ25 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ወርክሾፕ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ እድገት የ25 ሚሊየን ዩሮ ፕሮጀክት የማስጀመሪያ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው ።
ፕሮጀክቱ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና በጀርመን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ድርጅት (ጂአይዜድ) የተዘጋጀ ሲሆን÷ ለ4 ዓመታት የሚቆይና ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሺሰማ ገብረሥላሴ ÷የግሉ ዘርፍ በድህነት ቅነሳ ፈጣን እድገት ለማስመዝገብ እየተደረገ ባለው ሀገራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት እና ምርታማነትን በማሻሻልና የሥራ አጥን ቁጥር በመቀነስ የራሱ ድርሻ እንዳለው ጠቅሰዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለግሉ ዘርፍ እድገት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው÷ በተለይም የማምረቻ የኢንደስትሪ ዘርፉን እድገትና ተወዳዳሪነት ለማሻሻል እየተሠራ ነው ብለዋል።
የግሉ ዘርፍ መር የሆነ ኢኮኖሚ ለመፍጠር በቅንጅት እየተሠራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታ ው÷ የጀርመን መንግሥት በጂአይዜድ በኩል ለግሉ ዘርፍ እድገት ላለፉት ስድስት ዓመታት ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ በሥራ እድል ፈጠራ በገቢ እና በእሴት ጨማሪ ምርቶች ሚናቸውን እየተወጡ ለሚገኙ ጀማሪ፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ የጀመረው ፕሮጀክትም የሚበረታታ ነው ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡
በመድረኩ ጀርመን በኢትዮጵያ ለግሉ ዘርፍ እድገት አስተዋጽኦ አድርጋለች መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!