Fana: At a Speed of Life!

የፍቅር ጥያቄዬን አልተቀበለችኝም በማለት ወጣቷን በስለት ወግቶ የገደለው ወጣት በእስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 5፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍቅር ጥያቄዬን አልተቀበለችኝም በማለት ወጣቷን በስለት ወግቶ የገደለው ወጣት በ19 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።
ተከሳሽ ህፃኑ አብርሃም የተባለው ወጣት ሟች ውዴ ንጉሴ ጋር አንድ መንደር እንደሚኖሩ እና በቆይታቸው ከሟች ፍቅር እንደያዘው እና የፍቅር ጥያቄም እንዳቀረበላት በችሎቱ ተመላክቷል፡፡
ሟች ውዴ ንጉሴም በወቅቱ ለፍቅር ዝግጁ አለመሆኗን እና ለትምህርቷ ቅድሚያ እንደምትሰጥ ለገዳዩ ማስረዳቷንም ነው አቃቤ ህግ ያስረዳው፡፡
በዚህም ወጣቱ በበቀል ስሜት በመነሳሳት ታህሳስ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ በሚዛን አማን ከተማ ኮመታ ቀበሌ ውስጥ የግል ተበዳይን በስለት ወግቶ መግደሉን የአካባቢው ፖሊስ ማረጋገጥ መቻሉም ተመላክቷል፡፡
ፖሊስ ወጣቱን በቁጥጥር ስር በማድረግ ቃሉን ተቀብሎ ክስ እንዲመሠረትበት ለዐቃቤ ህግ የላከ ሲሆን፥ ከፖሊስ የደረሰዉን የምርመራ መዝገብን በማጣራት የቤንች ሸኮ ፍርድ ቤት ወጣት ህፃኑን አብርሃምን ጥፋተኛ ብሎታል፡፡
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰሞኑን በዋለው ችሎት ሌሎችን ያስጠነቅቃል ተከሳሹን ያስተምራል በሚል ተከሳሽ ህፃኑ አብርሃምን በ19 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.