Fana: At a Speed of Life!

ለላፕሴት ፕሮጄክት ተግባራዊነት አባል ሃገራት ጥረታቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን፣ ኬንያን እና ደቡብ ሱዳንን የሚያስተሳስረው የላፕሴት ፕሮጄክት ተግባራዊነት አባል ሃገራት የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማት ከፍተኛ ተወካይና የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ጥሪ አቀረቡ።
በኬንያ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር መለስ አለም ከራይላ ኦዲንጋ ጋር ተወያይተዋል።
በዚህ ወቅትም ራይላ ኦዲንጋ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ስትራቴጂክ አጋር መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
አያይዘውም ሃገራቱ ያላቸውን እምቅ አቅም ለመጠቀም ያላሰለስ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
መነሻውን ላሙ ወደብ ያደረገውና ኢትዮጵያ፣ ኬንያን እና ደቡብ ሱዳንን የሚያስተሳስረው የትራንስፖርት መሰረተ ልማት በቀጠናው ያለውን ሁኔታ የሚቀይርና ሃገራቱን የሚያቀራርብ ትልቅ ፕሮጀክት መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከዚህ አንጻርም አባል ሃገራቱ ለፕሮጄክቱ ተግባራዊነት አስፈላጊውን ጥረት ሊያደርጉ ይገባልም ነው ያሉት።
አምባሳደር መለስ አለም በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ለፕሮጄክቱ ተፈጻሚነት ቁርጠኛ ናት ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.