1 ሺህ 86 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ አረቢያ ችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 86 ዜጎች በዛሬው ዕለት ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ፡፡
ወደ አገራቸው ከተመለሱት ዜጎች ውስጥ 330 ሴቶች እና 80 የሚሆኑት ደግሞ ህጻናት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ እንዲሄዱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነው ዜጎችን የመመለስ ስራ ቁጥራቸው ከ8 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል፡፡