Fana: At a Speed of Life!

ለፋሲካ እና ለኢድ አልፈጥር በዓል መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ ዝግጅት ተደርጓል-ኤጀንሲው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለፋሲካ እና ለኢድ አልፈጥር በዓል መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን የግብይት ሰንሰለቱን በጠበቀ መልኩ በሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል ለህብረትሰቡ ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ለበዓሉ ለእርድ የሚሆኑ እንስሳትን ለማስመጣት የገበያ ትስስር እየተፈጠረ መሆኑን የገለጹት በኤጀንሲው የግብይት ዳይሬክተር ወይዘሮ ደብሪቱ ለአለም ÷ ከ6 ቀናት በኋላ እንስሳትን እናስገባለን ብለዋል።
ዘይት፣ስኳር እና የመሳሰሉ ግብዓቶችም ከ4 ቀን በኋላ በአዲስ አበባ በሚገኙት በ148 መሰረታዊ የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ይሰራጫሉ ነው ያሉት።
ለበዓሉ የሚሰራጩ መሰረታዊ የፍጆታ አቃዎች ተደራሽነትና ክፍፍል ላይ የፍትሀዊነት ችግሮች እንዳይኖሩ ክትትል ይደረጋልም ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አደም ኑሪ በበኩላቸው÷ ስርጭቱ በተስተካከለ መልኩ ተደራሽ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሰራር አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.