“ምግቤን ከጓሮዬ” የከተማ ግብርና ልማት እንቅስቃሴ በሐረሪ ክልል በይፋ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ” ምግቤን ከጓሮዬ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የከተማ የግብርና ልማት እንቅስቃሴ እንደ ሐረሪ ክልል በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡
በክልሉ በሚገኙ ሶስት ወረዳዎች ከ36 ሄክታር መሬት በላይ ለማልማት መታቀዱ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።
ዓላማውን የምግብ ፍጆታ ፍላጎትን በከተማ አካባቢ ለማማሏት ያደረገው ይህ የከተማ የግብርና ልማት ስራ በኢትዮጵያ የተከሠተውን የኑሮ ውድነት ለማስታገስ ፍላጎትን እና አቅርቦትን ለማጣጣም የከተማ ግብርና ወሣኝ መሆኑን በመረዳት ወደ ትግበራ መግባት አስፈላጊ መሆኑን የክልሉ የግብርና ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሻሜ አብዲ ተናግረዋል፡፡
ከጓሮ ልማት የሚጠበቀው ውጤት የከተማው ህብረተሰብ ከሸማችነት ወጥቶ አምራችነቱን አጎልብቶ የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ ማስቻል በማለት አቶ ሻሜ አብዲ ገልጸዋል ።
በቲያ ኑሬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!