የሀገር ውስጥ ዜና

የኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎችን ለሚያገናኘው የአርጆ‐ጉደቱ‐ጅርማ‐ሶጌ መንገድ ግንባታ የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

By Tibebu Kebede

October 21, 2019

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን በዲጋ ወረዳ የአርጆ ጉደቱ ጅርማ ሶጌ 46 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።

የመሰረት ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሀሰን እና የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡመድ ኡጁሉ ነው በጋራ የተቀመጠው መንገዱ 392 ሚሊየን ብር የተመደበለት ሲሆን፥ ወጪውን የኦሮሚያ ክልል መንግስት እንደሚሸፍነው ተገልጿል።