የሀገር ውስጥ ዜና

በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸዉ የህክምና ተቋማት 123 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ተደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

April 14, 2022

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ውድመት ለደረሰባቸዉ የአማራ ክልል ስምንት ዞኖች 123 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ድጋፍ ተበረከተ፡፡

ድጋፉ የተደረገው ዩኤስ ኤይድ ትራንስፎርም ፕራይመሪ ሄልዝ ኬር አክቲቪቲ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በፓዝ ፋይንደር አማካይነት ነው።

በከሚሴ ከተማ ለኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ድጋፍ በተደረገበት  ወቅት÷ የድርጅቱ የቴክኒክ ዳይሬክተር ዶክተር ሉዋም ተሾመ እንደተናገሩት፥ ይህ ድጋፍ በዞኑ ከደረሰዉ ጉዳት አንፃር ትንሽ ቢሆንም የህክምና ተቋማቱ ችግር የተለየ በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ ነው።

ለዞኑ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና መስጫ መሰሪያዋች የተበረከተ ሲሆን፥ በሌሎችም ዞኖች ተመሳሳይ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ዑስማን አሊ በበኩላቸው፥  የተደረገልን ድጋፍ ችግራችንን የሚያስተነፍስ በመሆኑ በቀጣይም ድጋፋችሁ አይለየን ብለዋል።

በዞኑ በህወሓት ወረራ ወቅት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት በጤና ተቋማት ላይ የደረሰ መድረሱን ገልጸው፥ከሚፈለገው መጠን አንፃር እስካሁን ድጋፍ የተደረገው ከ1 ነጥብ 8 በመቶ በታች ነው ብለዋል።

በዘሩ ከፈለኝ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!