Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሜካናይዜሽን የሶስትዮሽ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ እና ኢትዮሊዝ ከተሰኘ ድርጅት ጋር ግብርናን ሜካናይዝድ ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን በግብርና ሚኒስቴር የእርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሳኒ ረዲ፣ የኢትዮሊዝ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ እና የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ጪምዶ አንጫላ ተፈራርመውታል።

ስምምነቱ ሰፋፊ መሬቶች ላይ ቴክኖሎጅን በመጠቀም በድህረ ምርት አሰባሰብ የሚያጋጥም የምርት ብክነትን በመቀነስ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ መቀየርን ኣላማው ያደረገ መሆኑን፥ በሚኒስቴሩ የእርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ አቶ ሳኒ ረዲ ተናግረዋል።

የኢትዮሊዝ ሰብሳቢ አቶ ግርማ ዋቄ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የብዙ መስህብ ባለቤት መሆኗን ጠቅሰው የግብርናውን ዘርፍ ለማሳደግ በድርጅቱ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

ድርጅቱ በዋናነት ግብርናን ሜካናይዝድ በማድረግ ምርትና ምርታማትን ለማሳደግ እንደሚሰራ ጠቁመው፥ በሙከራ ፕሮጀክቶች ላይ ስምንት ከፍተኛ ጀኔሬተር እና ዘጠኝ ትራክተር በመስጠት ስራ መጀመራቸውን እንዲሁም 48 ትራክተሮች ደግሞ በመግባት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በቀጣይም ድርጅቱ የሜካናይዜሽን ስራን አጠናክሮ በማስቀጠል ለአርሶ አደሮች የእርሻ መሳሪያዎች እና የተለያዩ የግብርና ግብአቶችን እንደሚቀርብም አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ጪምዶ አንጫላ ባደረጉት ንግግር፥ በግብርናው በኩል ያሉት ችግሮችን በመለየት 300 ወረዳዎች የኩታ ገጠም እርሻ እንዲጠቀሙ መደረጉን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ውስጥ እያንዳንዳቸው 9 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚያወጡ 10 ሙሉ የሜካናይዜሽን ሰርቪስ ሊሰጡ የሚችሉ ተቋማት መገንባታቸውን ከግብርና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.