Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከእስራኤል የፓርላማ አባላት እና የሕክምና ባለሙያዎች የልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በጽ/ቤታቸው የፓርላማ አባላትን እና የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተውን የእስራኤል የልዑካን ቡድንን ተቀብለው አነጋግረዋል።
የልዑካን ቡድኑ በእስራኤል የፓርላማ አባሉ አቶ ጋዲ ይባርከን የተመራ ሲሆን፥ የፓርላማ አባላትን እና የሕክምና ባለሙያዎችን ያካተተ ነው።
የልዑካን ቡድኑ በጎንደር አካባቢ ጉበኝት በማድረግ በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
አቶ ደመቀ መኮንን የልዑካን ቡድኑ በዚህ ወሳኝ ወቅት በአገራችን ጉብኝት ማድረጉን አድንቀዋል።
ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት መልሶ ለመገንባት ታሳቢ ያደረገው ይህ የእስራኤል የልዑካን ቡድን ውቅታዊ ጉብኝት፥ የሁለቱን ሀገራት የቆየ እና ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑንም ነው አቶ ደመቀ የገለጹት።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የልዑካን ቡድኑ በአጭር ጊዜ እቅዱ ቅድሚያ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቆማት መልሶ መገንባት እና ማደረጃት ላይ ሊሆን እንደሚገባ በውይይታቸው ላይ ትኩረት ሰጥተው አንስተዋል።
የልዑካን ቡድኑ ዘለቄታነት ባለው ዕቅዱ ከጥቁር አንበሳ ሪፈራል ሆስፒታል እና ከሌሎች የኢትዮጵያ የጤና ተቋማት ጋር በቅርበት የመስራት ፍላጎት እንዳለው መግለጹንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.