Fana: At a Speed of Life!

የመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አጠፋ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ዞን ሆቢቻ ወረዳ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
የሆብቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ህዝቅኤል ኦይዳ እንደገለጸት፥ በትናንትናው ዕለት በአካባቢው ከጣለው ከባድ ዝናብ ጋር ተቀላቅሎ የወረደው መብረቅ ሁለት ሰዎችን ገድሏል።
እንዲሁም በሌሎች ሶስት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን ምክትል ኢንስፔክተር ህዝቅኤል ተናግረዋል።
በመብረቅ አደጋው ህይወታቸው ያለፈው የ30 እና 35 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሰዎች ናቸው ብለዋል።
በአካባቢው የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የወረደው መብረቅ በመኖሪያ ቤቶችና አጥር ላይ ጉዳት ማድረሱንም የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።
በአካባቢው የዝናብ ወቅት እየደረሰ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከመሰል የተፈጥሮ አደጋዎች ራሱን እንዲጠብቅ ምክትል ኢንስፔክተር ህዝቅኤል አሳስበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.