ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሴቶችና የሕፃናት ማዕከልን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በ’ለደግ ሚድዋይፈ ኮሌጅ’ የተቋቋመውን የሴቶችና የሕፃናት ማዕከልን ጎብኝተዋል::
ለደግ ሚድዋይፍሪ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ድርጅት በአሁኑ ጊዜ 115 ወጣት ሴቶችን ከሁሉም ክልሎች አምጥቶና ሙሉ ወጪያቸውን ሸፍኖ የሚያስተምር እና ሥልጠናቸውን ሲያጠናቅቁም ተመልሰው አካባቢያቸውን እንዲያገለግሉ የሚያደርግ ተቋም ነው።
ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በጉብኝታቸው ወቅት ባደረጉት ንግግር ”በራስ ተነሳሽነት፣ በጡረታ ገንዘብና ዕርዳታ እንዲህ ያለ ሥራ ለመሥራት ከተቻለ ÷ ሁላችንም የአቅማችንን ያህል ከሠራን ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ፣ የሰው ሠራሽና የተፈጥሮ አደጋ ሰለባ የሆኑ ሴቶችን ለመርዳት ብሎም በእግራቸው እንዲቆሙ ለማድረግ ስለሚቻል ይህን የመፈጸም አደራና ግዴታ አለብን” ሲሉ አሳስበዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!