Fana: At a Speed of Life!

‘‘ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ’’ መርሐ ግብር ለመሳተፍ እንግዶች እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከትናንት ምሽት ጀምሮ ‘‘ከኢድ እስከ ኢድ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ’’ ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ እንግዶችን በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቀባበል ማድረግ መጀመሩን ጥምር ኮሚቴው ገልጿል።

የኮሚቴው ሊቀመንበር ኡስታዝ አቡበከር አሕመድና የኮሚቴው አባል ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ከፋና ብርድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ፥ ከተለያዩ ዓለማት የሚገኙ በርካታ ዜጎች በመርሃ ግብሩ ለመሳተፍ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ጀምረዋል ብለዋል።

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጣምራ የተዋቀረው ኮሚቴም ወደ ሀገር ቤት እየገቡ ለሚገኙ እና ለሚገቡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ግዴታዎቻቸውን የሚወጡባቸው መርሐ ግብሮችን አዘጋጅተዋል።

ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ የሚደረግባቸው መርሃ ግብሮችን ጨምሮ የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት ፍሰትን ሊጨምሩ የሚችሉ የጉብኝት መርሃ ግብሮች፣ ሲምፖዚየምና ታላቅ የአፍጥርና የሰላት ዝግጅቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው ተብሏል።

አዘጋጆቹ በመላው ዓለም ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ባስተላለፉት መልዕክት ፥ መርሐ ግብሩ ኢትዮጵውያን ያለንን ብዝሃነት ተቻችሎ፣ ተከባብሮና ተደጋግፎ የመኖር እሴቶቻችንን በሀገር ጉዳይ ላይ አንድ የሆነ አቋማችንን የምናሳይበት አጋጣሚ በመሆኑ ጥሪውን አክብራችሁ ወደ ሀገራችሁ ግቡ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

መርሐ ግብሩ በሁለት ምዕራፎች ተከፋፍሎ ከኢድ አጋማሽ እስከ ኢድ ማብቂያና አረፋን ተከትሎ የሚከናወን በሚል ተዘጋጅቷል።

በትእግስት ስለሺ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.