Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር አደም መሀመድ ከቱርክ ሲ ቪል አቪዬሽን ሃላፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቱርክ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር አደም መሀመድ እና በቱርክ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርያል ማናጀር ፋኪያ አብደርህማን ከቱርክ የሲቪል አቪዬሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር ጀነራል ፕሮፌሰር ዶ/ር ከማል ዬኩሱክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ከ100 ዓመት በላይ የቆየውን የሁለቱ አገራት ግንኙነት በቀጣይ አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

አምባሳደር አደም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ቀዳሚ አየር መንገድ መሆኑን አውስተዋል፡፡

አየር መንገዱ በሁለቱ አገራት በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፍ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ማብራራታቸውንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በሁለቱ አየር መንገዶች ባሳለፍነው ዓመት በተፈረመው ስምምነት መሰረት በእንጥልጥል ላይ ባሉ ጉዳዮች ውይይት በማድረግ ወደ ተግባር መቀየር አስፈላጊ በመሆኑ በሚቀጥለው ወር ወደ ኢትዮጵያ በመሄድ ከአቻቸው ጋር እንዲወያዩ ፕሮፌሰር ዶክተር ከማል ዬኩሱክን ጠይቀዋል።

ሁለቱ አየር መንገዶች ትልቁን አውሮፕላን እና ካርጎ በአዲስ አበባና በኢስታንቡል ለመጠቀም መስማማታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.