የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚያዝያ 9 ቀን ጀምሮ አውደ ርዕይ እና ባዛር አዘጋጀ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከሚያዝያ 9 ቀን እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ አውደ ርዕይ እና ባዛር ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
በአውደ ርዕዩ እና ባዛሩ 181 የጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች 10 መካከለኛ በማምረቻው ዘርፍ የተሰማሩ እንዲሁም 8 ተቋማት በድምሩ 199 ተሳታፊዎች ይስተናገዳሉ ተብሏል፡፡
በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቡድን መሪ ወይዘሮ አቦዘነች ነጋሽ እንደገለፁት÷ 50 በመቶ ኢንተርፕራይዞቹ የሴቶች ሲሆኑ አምስት ኢንተርፕራይዞች ደግሞ የአካል ጉዳተኞች ናቸው፡፡
አውደ ርዕዩ እና ባዛሩ 22 ሺህ ሰዎች ይጎበኙታል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሯ 4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዋናነትም የገበያ ትስስርን ለማጠናከር እና ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በምርትና በጥራት መሻሻሎችን ማሳየታቸውን ለማረጋገጥ ታስቦ መዘጋጀቱ ተመላክቷል፡፡
አውደ ርዕዩ ጀሞ ቁጥር 1 አደባባይ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በፈትያ አብደላ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!