Fana: At a Speed of Life!

በክልል ከተሞች ለተለያዩ ጉዳዮች ያለደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ ህብረተሰቡን እያማረረ መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በክልል ከተሞች በተለያዩ ስያሜዎች በመንግስት አካላት ያለደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ ህብረተሰቡን በከፍተኛ ደረጃ እያማረረ መሆኑ ተመላከተ፡፡
ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አስተያየታቸውን የሰጡ የሻሸመኔ፣ ጅማ እና የሌሎች ክልል ነዋሪዎች ለአካባቢ ልማት፣ ለመከላከያ፣ ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ እየተባለ የተሰበሰበው ገንዘብ ምንም ዓይነት የመቆጣጠሪያ መንገድ ባለመኖሩ ለግለሰቦች መበልፀጊያ ሆኗል ብለዋል።
ከቀበሌ እስከ ዞን ባሉ የመንግስት መዋቅር ሰራተኞች እና አመራሮች በየጊዜው የተለያዩ ስያሜዎችን እየቀያየሩ ገንዘብን ያለደረሰኝ የመሰብሰቡ ሂደት በርክቷል ነው ያሉት።
በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ሱራፌል ጌታሁን÷ መሰል ተግባራት እየተስፋፋ መምጣት በህዝቡ ዘንድ የመልካም አስተዳደር ችግርን ፈጥሯል።
በሀገሪቱ ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት ያለው አሰራር ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ህዝብ ከመንግስት ጋር በመተባበር በልማት ላይ የሚያደርገውን ተሳትፎ ያቀጭጫል ነው ብለዋል።
በገቢዎች ሚኒስቴር የህግ አገልግሎት ዳሬክተር አቶ አበረ አስፋ÷ በህግ ግዴታ የተጣለባቸው የአገልግሎት ክፍያ፤ ታክስና ግብር ጨምሮ ወደ መንግስት ካዝና የሚገባ ገንዘብ ከአንድ ሳንቲም ጀምሮ በደረሰኝ እንዲሰበሰብ ህግ ያስገድዳል ብለዋል።
ሆኖም መንግስት በሀገር አቀፍም ይሁን በቀበሌ ደረጃ ለበጎ አድራጎት ከህዝብ ገንዘብ የመሰብሰቢያ አሰራር እና ሕግ ግን የለም ነው ያሉት።
በዚህም የፌደራል መንግስትም ይሁን የአካባቢ የመንግስት መዋቅር ህዝብ የሚሳተፍበት እርዳታ ሲፈለግ እንዴት እንደሚፈጸም ፣ ማን ገንዘቡን እንደሚሰበስብ፣ በማን ቁጥጥር እንደሚደረግበት እና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚዘረዝር ሕግ መውጣት አለበት ብለዋል።
በበላይ ተስፋዬ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.