ዓለምአቀፋዊ ዜና

የሩሲያ የጦር መርከብ በጥቁር ባህር ሰጠመች

By Meseret Awoke

April 15, 2022

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የሩሲያ የጦር መርከብ በጥቁር ባህር ሰጠመች።

የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፥ ሞስኮቫ የተባለችው የሩሲያ ሚሳኤል ተሸካሚ መርከብ ልትሰጥም የቻለችው መርከቧ የተሸከመችው ጥይት በመፈንዳቱ እና የመርከቧ ውስጠኛ ክፍል በእሳት በመጎዳቱ ነው።

በወቅቱ የመርከቧ ሰራተኞች በአቅራቢያ ወዳሉ መርከቦች በመሄድ ራሳቸውን ከአደጋ ማትረፋቸው ተነግሯል።

የጦር መርከቧ ለጥገና ጉዞ ጀምራ የነበረ ቢሆንም መሃል ላይ ግን ሰጥማለች ነው የተባለው።

ዩክሬን በፊናዋ የሩሲያን የጦር መርከቧን በሚሳኤል መትቼ እንድትሰጥም ያደረኩት እኔ ነኝ ስትል፥ አሜሪካ የመርከቧን መስመጥ ምክንያት እስካሁን አላረጋገጥኩም ብላለች።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!