በመተከል ዞን 247 የሚሆኑ የጉህዴን ታጣቂዎች ለመንግሥት እጅ ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ 247 የሚሆኑ የጉህዴን ታጣቂ ዎች እጅ መስጠታቸውን የዳንጉር ወረዳ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ፡፡
የወረዳው ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሻለቃ ደምስ ዳኘ÷ በወረዳው የአሸባሪውን ህውሓት ተልዕኮ ተቀብለው የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) በሚል ስም ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 247 ታጣቂዎች ለፀጥታ ኃይሉ በሰላማዊ መንገድ እጅ መስጠታቸውን ገልጸው÷ ከነዚህም ውስጥ በዛሬው ዕለት 57 ሽፍቶች ከነትጥቃቸው መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡
የጥፋት ኃይሎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ ከቀረበላቸው የሰላም ጥሪ ባለፈ÷ በመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት ቅንጅት ሕግን ለማስከበር እየተወሰደ ባለው የኦፕሬሽን ሥራ ብዙዎች እጅ እየሰጡ መሆኑንም ጨምረው መግለጻቸውን ከመተከል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከጦርነትና ከግጭት የሚገኝ ትርፍ ባለመኖሩ ቀሪዎችም በተመሳሳይ ከነትጥቃቸው እጅ እንዲሰጡ የዳንጉር ወረዳ ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢና የምዕራብ ዕዝ 7ኛ መካናይዝድ ጦር የብረት ለበስ ጦር አዛዥ ሻለቃ ደምስ ዳኘ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!