Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ዙር የልጅነት ልምሻ ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ክልሎች እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 7፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ሁለተኛው ዙር የልጅነት ልምሻ (ፖሊዮ) ክትባት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ክልሎች መሰጠት ጀምሯል፡፡
ክትባቱ በጋምቤላ ክልል እየተሰጠ ሲሆን ዕድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ 140 ሺህ ህፃናት ክትባቱ የሚሰጥ መሆኑን የክልሉ ምክትል ጤና ቢሮ ሃላፊ አቶ ታች ኮንግ ተናግረዋል፡፡
በክትባት መርሐ ግብሩ በርካታ የጤና ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች በሁሉም ወረዳዎችና የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ተሰማርተው ክትባቱን እየሰጡ እንደሚገኝ ምክትል ሃላፊው አስረድተዋል።
በተመሳሳይ ክትባቱ በሐረሪ ክልል መሰጠት የጀመረ ሲሆን በክልሉ ከ56 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑ ህፃናትን ለመከተብ መታቀዱን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢብሳ ሙሳ ገልፀዋል፡፡
ክትባቱ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ቤት ለቤት በመዟዟርና በትምህርት ቤቶች እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንደሚሰጥ መናገራቸውን የየክልሎቹ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል።
ቀደም ሲል የአማራ ክልል ሁለተኛ ዙር የልጅነት ልምሻ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 10 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከ2 ሚሊየን በላይ ህፃናትን ለመከተብ እንዳቀደ መግለጹ ይታወሳል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.