Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከቡና ወጪንግድ ከ894 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከቡና ወጪ ንግድ ከ894 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር ዛሬ በሰጡት መግለጫ ÷ ባለስልጣኑ ከቡና ምርት ጀምሮ እስከ ኤክስፖርት ድረስ የተቀናጀ የቁጥጥር ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።
በተያዘው ዓመት ከ210 ሺህ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጪ መላኩን ገልፀው ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ43 ነጥብ 66 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ተናግረዋል።
በዚህም ከ894 ሚልየን ዶላር በላይ የውጪ ምንዛሪ መገኘቱንና ገቢው ከተያዘው እቅድ አንጻር 133 በመቶ አፈጻጸም እንደተመዘገበበት ገልፀዋል።
ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 74 ነጥብ 52 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረው በቀጣይም ባለስልጣኑ ገቢውን ወደ ቢሊየን ዶላር ለማሳደግ እንደሚተጋ ጠቁመዋል።
የምርት ጥራትን ማሳደግ፣ ግብይትን ማዘመን እና አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስርዓቶች መዘርጋታቸው ለዕቅዱ መሳካት ወሳኝ ሚና ማበርከታቸውንም ነው የገለጹት፡፡
ባለስልጣኑ የቁጥጥር ስርዓቱ የሚመራበት ሶፍት ዌር በማበልጸግ ተግባራዊ ማድረጉም ለዕቅዱ ስኬት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በሌላ በኩል በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ እና በመጋዘን ተከማችተው በተገኙ እንዲሁም የምርት ግብይት በተላለፉ አካላት ላይ በተወሰደ እርምጃ ከ83 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ ለመንግስት ገቢ መደረጉንም መጠቆማቸውን ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.