Fana: At a Speed of Life!

የባሕርዳር ከተማ በጎ አድራጎት ማኅበር ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የዓይነት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባሕርዳር ከተማ በጎ አድራጎት ማኅበር በግጭቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሰቆጣ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች ግምቱ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ማኅበሩ 350 ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ 170 ኩንታል ማካሮኒ ፣ሌሎች ከ400 መቶ ኩንታል በላይ የሚገመቱ ምግብ ነክ ቁሳቁስ፣የንፅህና መጠበቂያዎች እና አልባሳት በመጠለያ ጣቢያው በመገኘት አስረክቧል፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በዋግኽምራ በፈጠረው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ተጎጂ ለሆኑ ወገኖች በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ከሚኖሩ ምግባረ-ሠናይ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተሰበሰበ ድጋፍ መሆኑንም የማኅበሩ አስተባባሪ ወጣት መታገስ ገብረ እግዚአብሔር ገልጸዋል፡፡

ድጋፉ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ማሳወቃቸውንም ከዋግኽምራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.