Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በታይዋን የውስጥ ጉዳይ ላይ የምታደርገው ትንኮሳ በእሳት እንደ መጫዎት ይቆጠራል – ቻይና

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ፓርላማ አባላትን ያካተተ የልዑካን ቡድን በታይዋን ጉብኝት ማድረጉን ተከትሎ ቻይና በታይፔ አቅራቢያ ወታደራዊ ልምምድ እያደረገች መሆኗ ተገልጿል፡፡
 
የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷የአሜሪካ ህግ አውጭ አካላት በታይዋን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ደሴቷ መግባታቸው ግልጽ የሆነ የጠብ አጫሪነት እርምጃ ነው ብሎታል፡፡
 
“ድርጊቱን በእሳት እንደ መጫዎት እንቆጥረዋለን” ያለው የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር÷ አሜሪካ በታይዋን የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት መሰል ግጭት ቀስቃሽ ድርጊቶች ከመፈጸም እንድትቆጠብ አሳሰስቧል፡፡
 
የአሜሪካ ፓርላማ አባላት በታይዋን እያደረጉ ያሉትን “ሴራ አዘል” ጉብኝት ተክትሎም ቤጂንግ በታይፔ ደሴት አቅራቢያ መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ መጀመሯን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
 
ወታደራዊ ልምምዱ በቀጠናው የተፈጠረውን ውጥረት ለመቆጣጠር እና የቻይናን ሉዓላዊ ግዛት ለማስከበር ያለመ መሆኑም ተገልጿል፡፡
 
በወታደራዊ ልምምዱ ተዋጊ ጀቶች፣ የጦር መርከቦች፣ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች፣ መቃወሚያዎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች መሳተፋቸው ተመላክቷል፡፡
 
አሜሪካ በበኩሏ ቻይና ከታይዋን ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሃይል አማራጭን ከመጠቀም ይልቅ በሰለጠነ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ልትፈታ ይገባል ማለቷን አናዶሉ ዘግቧል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.