የሀገር ውስጥ ዜና

በደሴ ከተማ ” ኑ አብረን በጋራ እናፍጥር” በሚል መሪ ቃል ታላቅ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሃ ግብር ተካሄደ

By Feven Bishaw

April 15, 2022

 

የደሴ ከተማ ህዝባዊ መጅሊስ ሰብሳቢ ሼህ እንድሪስ በሽር ÷ ታላቁ የኢፍጣር መርሃ ግብር የተዘጋጀው በጦርነቱ ምክንያት ህዝባችን ላይ የደረሰውን የስነልቦና ስብራት በማከም ወደነበረበት ልዕልና ለመመለስና የከተማችን ህብረተሰብ የሚታወቅበትን አንድነትና አብሮነት ማጽናትን አላማ አድርጎ ነው ብለዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው÷መርሃ ግብሩ መልካም እሴቶችን የሚያጎለብት በመሆኑ ማህበራዊ ቅርርብ ለመፍጠር ሚናው የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የክርስትና እምነት ተወካዮችም በመርሃ ገብሩ ተገኝተው “የኢፍጣር መርሃ ግብሩ አብሮነታችንን የሚያጎለብትና የወሎን ተምሳሌትነት በአደባባይ የምናሳይበትን እድል የፈጠረ ነው” ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተውናል።

በሌላ በኩል መንግስት የዘንድሮውን የረመዳን ወር በመላው ዓለም የሚገኙ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ እንዲያከብሩ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ‘ከዒድ እስከ ዒድ’ በሚል መሪ ሐሳብ ወደ ደሴ ከተማ የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በዘሩ ከፈለኝ