ስፓርት

የወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ቡድን እገዳው ተነሳለት

By Tibebu Kebede

February 28, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ክለብ ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ ባለፈው ዓመት ክለቡን ካገለገሉት ስምንት ተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የፍትህ አካል ያስተላለፈውን ውሳኔ በተሰጣቸው ጊዜ መሰረት ባለመፈፀማቸው ቡድኑን ከማንኛውም ውድድር ማገዱ ይታወሳል።

ነገር ግን ተጫዋቾቹ ለፌዴሬሽኑ ዛሬ በፃፉት ደብዳቤ ደመወዛቸው እንደተከፈላቸውና ክለቡ ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ባሰባሰቡት ፊርማ አረጋግጠዋል።

ይህን ተከትሎም ፌዴሬሽኑ ክለቡ ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታውቋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ! https://t.me/fanatelevision