ሩሲያ የዩክሬንን የሚሳኤል ማምረቻ ማውደሟን አስታወቀች
አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ኪየቭ አቅራቢያ የሚገኝን የዩክሬን ሚሳኤል ማምረቻ ማውደሟን አስታውቃለች፡፡
ጥቃቱ የተፈፀመው ዩክሬን የሩሰያን የጦር መርከብ “በሚሳኤል መትቼ አስጥሚያለሁ “ ማለቷን ተከትሎ ሲሆን፥ ሞስኮ ኪየቭ ላይ ተጨማሪ ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል አስጠንቅቃም ነበር።
ሩሲያ በፈፀመችው ጥቃት በኬየቭ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚገኘው የሚሳኤል ማምረቻው የአስተዳደር ህንፃ እና የማምረቻ ወርክሾፕ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ተመላክቷል፡፡
ሩሲያ ቀደም ሲል ዩክሮቦሮንፕሮም እና ኔፕቱን የተባሉ ሚሳኤሎችን የሚያመርተውን የዩክሬን ሚሳኤል ማምረቻ ፋብሪካን ለመምታት በካሊባር ባህር ላይ የተጠመደውን የረጅም ርቀት ሚሳኤሎቿን እንደምትጠቀም ገልፃ ነበር፡፡
የዩክሬን ባለስልጣናት ስለጉዳቱ መጠን ዝርዝር መረጃ ከመስጠት የተቆጠቡ ሲሆን ፥ ትናንት ከሩሲያ የተሰነዘሩ ሁለት የሚሳኤል ጥቃቶች ግን ኪየቭ አቅራቢያ ጉዳት ማድረሳቸውን ገልፀዋል፡፡
በተጨማሪም ሩሲያ ተጨማሪ ጥቃት ልትፈፅም እንደምትችል በማስጠንቀቅ ወደ ዋና ከተማዋ ኪየቭ ለመመለስ የሚያስቡ ዩክሬናውያን ባሉበት እንዲቆዩ ማሳሰባቸውን አር ቲ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!