Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎችን የደንብ ልብስ ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ የከተማዋን የትራፊክ እንቅስቃሴ ሰላማዊ እና ተቀባይነት ያለው ለማድረግ የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የሚለብሱት የደንብ ልብስ ይፋ አድረጓል፡፡
 
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ÷ የደንብ ልብሱ የቁጥጥር ባለሙያዎቹ በግንዛቤ የተደገፈ ጥብቅ የትራፊክ ቁጥጥር በማድረግ በትራፊክ ግጭት አደጋ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቀነስ እና ለማስቀረት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
 
ኤጀንሲው ይፋ ያደረገው የትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች የደንብ ልብስ የቁጥጥር ስራውን የበለጠ ለማጠናከር የሚያግዝ ግብዓት ሲሆን÷ ባለሙያዎቹ እስከ አሁን የደንብ ልብስ ስላልነበራቸው አንፀባራቂ ብቻ ለብሰው ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡
 
ይህም ከሌሎች ተቋማት ሰራተኞች እና የተለያዩ አካላት ጋር ተመሳሳይ በመሆኑ በተለይ አሽከርካሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር እና ይፋ የተደረገው የደንብ ልብስም ይህን ቅሬታ የሚፈታ ነው ብለዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም የደንብ ልብሱ ከዚህ በፊት ተመሳሳይ አንፀባራቂ በመልበስ አሽከርካሪን አስቁሞ ተሽከርካሪውን ይዞ እስከ መሰወር የደረሰ የዘረፋ እና የሌብነት ተግባርን እና መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያግዝ ነው መባሉን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.