Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በአሻባሪው ህወሓት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የጤና ተቋማት ወደ አገልግሎት መስጠት እየተመለሱ ነው- የክልሉ ጤና ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው እና ወራሪው የህወሓት ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ ጤና ተቋማት ባለሙያዎች ባሳዩት ቁርጠኝነት አገልግሎት መስጠት እየጀመሩ መሆኑን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ገልጿል፡፡

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የ2014 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በኮምቦልቻ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የቢሮው ሃላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ ÷በክልሉ አሸባሪው ህወሓት በጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ያደረሰ ቢሆንም÷ ተቋማቱ በተለያዩ አካላት ርብርብ ወደ መደበኛ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት እየተመለሱ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በሚቀጥሉት 3 ወራት በዘመቻ መልክ በጤናው ዘርፍ የሚታየውን አገልገሎት አሰጣጥ የተሻለ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

በተለይም የጤና ኤክስቴንሽንና የወረዳ ትራንሰፎርሜሽን ስራዎች ትኩረት ተሰጥቶባቸው እንደሚሰራ የገለጹት ሃላፊው ÷ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በሽብር ቡድኑ የወደሙና እስከ አሁን ያልተተኩ ግብዓቶችን በማሻሻል የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

የጤና ባለሙያዎች አሁንም በትኩረት በመስራት የጤናውን ዘርፍ የተሻለ ለማድረግ እንደወትሮው ሃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በክልሉ 40 ሆሰፒታሎች 453 ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም 1 ሺህ 870 የጤና ኬላዎች በሽብር ቡድኑ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ተቋማቱ አሁን ላይ የእናትና ህጻናትን እንዲሁም መሰል ድንገተኛ አገልገሎት እየሰጡ ሲሆን÷ በከፊል እየሰሩ የሚገኙትን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለማሰገባት እየተሰራ ነው ተብሏል።

በከድር መሀመድ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.