Fana: At a Speed of Life!

“ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻችን ለሰላማችን እና ለአብሮነታችን” በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻችን ለሰላማችን እና ለአብሮነታችን” በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት ተካሄደ።

በዓለም የእርቅና ሰላም ግብረሰናይ ድርጅት አማካይነት የተካሄደው ውይይት ዋና ትኩረቱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ለሰላም ባላቸው ፋይዳ ላይ ሲሆን ፥ በመድረኩ የሀገር -በቀል እውቀቶች ጠቀሜታ ላይም ውይይት ተደርጓል።

“የሰላማችን እጦትና የፀባችን መንስኤ አለማወቅ ነው” ያሉት የዓለም እርቅና ሰላም ግብረሰናይ ድርጅት የበላይ ጠባቂ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሱራፌል ሲሆኑ፥ እኛ የሃይማኖት መሪዎችም ተከታዮቻችንን የማስተማርና የማሳወቅ ግዴታ አለብን ብለዋል።

የሰላም እጦት ችግር የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም ፈተና ሆኗል ያሉት በመድረኩ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሀገር- በቀል እውቀቶች ተመራማሪው ዶክተር ሰለሞን በላይ ሲሆኑ ፥ ባለፈው አንድ ወር ብቻ በመላው ዓለም የተካሄዱት ግጭቶች በ6 ነጥብ 9 በመቶ መጨመራቸውንና ሞት ደግሞ በ5 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የተፈጠረውን የሰላም እጦት ለመመለስ የሀገር-በቀል እውቀትና የሃይማኖት ትምህርቶችን በመስጠት በርትቶ መስራት ይገባል ብለዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ የዓለም የእርቅና ሰላም ግብረሰናይ ድርጅት የበላይ ጠባቂ ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ፣ የድርጅቱ የቦርድ አባላት ቀሲስ መዝገቡ ካሳ፣ ልዑል ራስ መንገሻ ስዩምና ፕሮፌሰር አሕመድ ዘካሪያን ጨምሮ በርካታ የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.