Fana: At a Speed of Life!

ፋና ላምሮት የባለ ተሰጥኦ የድምጻውያን ውድድር 10ኛ ምዕራፍ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፋና ቴሌቪዥን የሚዘጋጀውና ተወዳጁ የፋና ላምሮት የባለ ተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር 10ኛ ምዕራፍ ዛሬ ተጀመረ።

ፋና ላምሮት ከአዳዲስ ተወዳዳሪዎችና ባለተሰጥኦዎች ጋር በቀጥታ ስርጭት የጀመረ ሲሆን፥ በሁለት ምድብ የተከፈሉት የምዕራፍ 10 ተወዳዳሪዎች 12 ናቸው፡፡

የምድብ አንድ ስድስት ተወዳዳሪዎች በቀጥታ ስርጭት ራሳቸው በመረጧቸው ሙዚቃዎች በሶስት ዙር ተወዳድረዋል።

ለዘጠኝ ሳምንታት የሚቆየው የምዕራፍ 10 የፋና ላምሮት የባለተሰጥኦ ድምጻውያን ውድድር መጨረሻ የሚቀሩ አራት የምዕራፉ ተፋላሚዎች እንደየደረጃቸው የ500 ሺህ ብር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

አንደኛ ደረጃን ላገኘ የ200ሺህ ብር፣ 2ኛደረጃ 150 ሺህ ብር፣ 3ኛ ደረጃ 100 ሺህ ብር እና 4ኛ ደረጃን ያገኘ የ50 ሺህ ብር ሽልማት አሸናፊ ይሆናሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ የፍጻሜ ተወዳዳሪዎች ለተናፋቂው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ፡፡

በቀጥታ ስርጭት የተጀመረው የምዕራፍ 10 የፋና ላምሮት ውድድር ተመልካቾች ወደ 8222 አጭር የፅሁፍ መልዕክት በመላክ ለሚደግፉት ተወዳዳሪ ድምፅ መስጠት ይችላሉ።

ባለፈው የምዕራፍ 9 ፋና ላምሮት የባለተሰጥዖ ድምጻውያን ውድድር ፍጻሜ ከሁለት ሳምንት በፊት የተጠናቀቀ ሲሆን ፥ ተወዳዳሪዎች ራሳቸው በመረጧቸው እና ዳኞች በመረጡላቸው ሙዚቃዎች ተፈትነው ከአንድ እስከ አራት ለወጡት ተወዳዳሪዎቹ በአጠቃላይ የ500 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ድምጻዊ አሉላ ገ/አምላክ የ9ኛው ምእራፍ አሸናፊ መሆኑም ይታወሳል።

በፈቲያ አብደላ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.