Fana: At a Speed of Life!

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተሳካ የሮኬት ማስወንጨፍ ሙከራ አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሦስተኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የአፄ ቴዎድሮስን 154ኛ ዝክረ ሰማዕት ምክንያት በማድረግ አሞራ ገደል በተባለ ሥፍራ የተሳካ የሮኬት ማስወንጨፍ ሙከራ አካሂዷል።

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ያደረገው ሙከራ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ፥ ባለፉት ዓመታት የተለያዩ የቴክኖሎጂ ምርምሮችን ሲያካሂድ መቆየቱን የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚደንት ዶክተር አነጋግረኝ ጋሻው ተናግረዋል።

ይህ ምርምር አድጎ ለሀገሪቷ የሕዋ ሳይንስ ምርምር አጋዥ እንዲሆን ተግባሩ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በተጨማሪም በዝክረ ሰማእት መታሰቢያ ዕለቱ የአፄ ቴዎድሮስን የመድፍ ሥራ የሚያስታውስ ምስለ ሴባስቶፖል መድፍ ተሰርቶ በደብረ ታቦር ከተማ የመተኮስ ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.